የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አተረጓጎም (Hermeneutics)

የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አተረጓጎም (Hermeneutics)

የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አተረጓጎም (Hermeneutics)-image

ስለ ሴሚናሩ

የእግዚአብሔርን ቃል “በትክክል የሚያስረዳ” (2 ጢሞ 2:15) አገልጋይና አማኝ ለመሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት በትክክል እንደሚያዝ መረዳት ወሳኝ ነው። ይህ ሴሚናር ከዘልማዳዊ ንባብ ወጥተን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ዐውድ፣ የሥነ-ጽሑፍ ዓይነት እና የቃላት ፍቺ በመመርመር፣ የጸሐፊውን ሐሳብ እንዴት ማግኘት እንደምንችል በተግባር የሚያስታጥቅ ነው።

በሴሚናሩ የሚዳሰሱ ዋና ዋና ርዕሶች፡-

  • ሦስቱ የትርጉም ምሰሶዎች (Contexts): አንድን ምንባብ ከመተርጎማችን በፊት ማወቅ ያለብን ታሪካዊና ባህላዊ ዳራ (Historical & Cultural Background)፣ ሥነ-መለኮታዊ ዐውድ (Theological Context) እና የሥነ-ጽሑፍ ዐውድ (Literary Context) ምን እንደሆኑ እናያለን ።
  • የሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶች አተረጓጎም (Genre Analysis): መጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ዓይነት ሥነ-ጽሑፍ የያዘ መጽሐፍ ነው።

    • ትረካዎችን (Narratives) እንዴት እናንብብ? (ታሪኩ እንዴት ይፈሳል? ገጸ-ባህርያት እንዴት ይሳላሉ?) ።
    • ግጥሞችንና መዝሙራትን (Poetry) እንዴት እንረዳ? (ጉድኝት/Parallelism እና ዘይቤያዊ አነጋገሮች) ።
    • መልእክታትን (Epistles) እንዴት እንመርምር? (የደብዳቤው መዋቅር፣ አላማ እና ዐውዳዊ ትርጉም) ።

  • የቃል ጥናት (Word Study): የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት በዘፈቀደ ከመተርጎም በመውጣት፣ ቃሉ በዚያ ዐውድ ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ፍቺ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል እና “የቃል ጥናት ስህተቶችን” (Fallacies) እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል እንማራለን ።
  • ከምንባብ ወደ ሕይወት (Contextualization): የጥንቱን መልእክት ሳይበረዝ ለዛሬው ትውልድ እንዴት ማዛመድ ይቻላል? “ምን ሊባል ተፈልጐ ነው?” (Exegesis) ከሚለው ተነሥተን “ለእኛ ዛሬ ምን ይለናል?” (Application) ወደሚለው የሕይወት ለውጥ እንዴት እንደምንሸጋገር እናያለን ።

ይህ ትምህርት ለማን ነው?

  • ለሰባኪዎችና መምህራን፦ ስብከታቸውና ትምህርታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ለሚፈልጉ።
  • ለጉባኤ መሪዎችና አገልጋዮች፦ ቃሉን በንጽህና እና በትክክል ለመረዳት ለሚተጉ።
  • ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፦ የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ለሚሻ ማንኛውም አማኝ።

ማሳሰቢያ

ይህ ሴሚናር የንድፈ-ሐሳብ (Theory) ትምህርት ብቻ ሳይሆን፣ ተሳታፊዎች በራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን አውጥተውና አውርደው እንዲያጠኑ የሚያግዝ ተግባራዊ ልምምድ (Practical Exercises) የተካተተበት ነው።

ቃሉን በትክክል ለመረዳትና ለማስረዳት ራስዎን ያዘጋጁ! ፕሮግራም ያስይዙ።