የመንግሥቱ ደንብ፡ የተራራው ስብከት

የመንግሥቱ ደንብ፡ የተራራው ስብከት

የመንግሥቱ ደንብ፡ የተራራው ስብከት-image

ስለ ሴሚናሩ

"የተራራ ላይ ስብከት" የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ጫፍ እና የክርስትናዊ ሥነ-ምግባር መሠረት ነው። ብዙዎቻችን እነዚህን ምንባባት (ማቴዎስ 5 - 7 ) ብናውቃቸውም፣ ወደ ጥልቀቱ ወርደን የመንግሥቱን የኑሮ ዘይቤ ምንነት ግን አልተረዳንም። ይህ ሴሚናር፣ ኢየሱስ በምድር ላይ ሊመሠርተው ስለመጣው መንግሥት ባህርይ፣ ስለ እውነተኛ ጽድቅ እና ስለ ኪዳኑ ሕዝብ አኗኗር ያስተማረውን ሕያው ቃል የምንመረምርበት ነው።

ይህ ትምህርት ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስሰውን የተለወጠ ማንነት እና በተግባር የሚገለጥ እምነትን እንድንላበስ ይጋብዘናል።

በሴሚናሩ የሚዳሰሱ ዋና ዋና ርዕሶች፡-

  • የመንግሥቱ ዜጎች ማንነት (The Beatitudes): "ብፁዓን" ተብለው የተጠሩት እነማን ናቸው? በመንፈስ ድሆች፣ የሚያዝኑ እና የዋሆች ለምን የመንግሥቱ ወራሾች ተባሉ?
  • ክርስቶስና ሕጉ (Christ and the Law): ኢየሱስ ሕግን ለመሻር ወይስ ለመፈጸም መጣ? "ተብሎ እንደተነገረ ሰምታችኋል... እኔ ግን እላችኋለሁ" የሚለው የሥልጣን ቃል፣ የብሉይ ኪዳንን ሕግ እንዴት ወደ ላቀ ደረጃ እንዳሸጋገረው እናያለን።
  • እውነተኛ ጽድቅ (True Righteousness): ከግብዝነት የጸዳ መንፈሳዊ ተግዳሮቶች ምን ይመስላሉ? የፈሪሳውያንን "ለሰው ለመታየት" አባዜ በማስወገድ፣ በስውር ለሚያይ አባት መኖር ምን እንደሚመስል እንማራለን።
  • የመንግሥቱ እሴቶች (Kingdom Values): ስለ ገንዘብ፣ ስለ ጭንቀት እና ስለ መፍረድ የተሰጡ ትምህርቶች። ሀብታችንን በሰማይ ማከማቸት እና አስቀድሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ ማለት ምን ማለት ነው?
  • ሁለቱ መንገዶች (The Two Ways): በጠባቡ ደጃፍ መግባት፣ የሐሰት ነቢያትን መለየት እና ቤትን በአለት ላይ መሥራት። የሰማነው ቃል ዋጋ የሚኖረው በተግባር ሲገለጥ ብቻ መሆኑን እናያለን።

ይህ ትምህርት ለማን ነው?

  • ለቤተክርስቲያን መሪዎች፡ ምእመናንን ክርስቶስን ወደ መምሰል (Christlikeness) ለመቅረጽ ለሚተጉ።
  • ለወጣቶችና አገልጋዮች፡ በዚህ ዘመን ካለው "የብልጽግና ወንጌል" እና "የግብዝነት ኑሮ" ተጠብቀው፣ የኢየሱስን እውነተኛ ፈለግ ለመከተል ለሚሹ።
  • ለማንኛውም ክርስቲያን፡ ክርስትናን እንደ ሃይማኖት ሳይሆን እንደ "ሕይወት ዘይቤ" ለመኖር ለሚፈልግ ሁሉ።

ማሳሰቢያ

ይህ ሴሚናር ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ ተራራ ላይ ያስተጋባውንና የዓለምን ታሪክ የቀየረውን ትምህርት፣ ለዛሬው ትውልድ በሚገባ እና በተግባራዊ መልኩ የሚያቀርብ ነው።

ሕይወትዎን በአለት ላይ ይገንቡ! እኛን በማነጋገር ፕሮግራም ያስይዙ።