ቅርጸ-መስቀላዊ አገልግሎት፡ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ጥሪና ክብር
(በ2ኛ ቆሮንቶስ መልእክት ላይ የተመሠረተ የአገልጋዮች ስልጠና)
ስለ ሴሚናሩ
በዘመናችን ስለ "አገልግሎት" ያለን ግንዛቤ በዝና፣ በገንዘብና በውጫዊ ስኬት መለኪያዎች ተበርዟል። ብዙዎች "ለዚህ ነገር የሚበቃ ማን ነው?" ብለው ከመጠየቅ ይልቅ፣ በራሳቸው ብቃት እየተመኩ ወንጌልን ወደ ንግድ ሸቀጥነት (Peddling) የቀየሩበት ጊዜ ላይ ነን። ይህ ሴሚናር፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ እንደሚያስተምረው፣ አገልግሎት ማለት የግል ስኬት መሰላል ሳይሆን "በክርስቶስ የድል ሰልፍ ውስጥ እንደተማረከ ደስተኛ ምርኮኛ" ሆኖ መገኘት እንደሆነ ያስረዳል። አገልጋዮች የራሳቸውን ዝና ሳይሆን "የተሰቀለውን ክርስቶስን" በመስበክ ፣ አገልግሎታቸው የመስቀሉን ቅርጽ (Cruciformity) እንዴት መላበስ እንዳለበት በሰፊው ይዳስሳል።
በሴሚናሩ የሚዳሰሱ ዋና ዋና ርዕሶች፡-
- የአገልግሎት ጥሪና ማንነት፦ እውነተኛ አገልጋይ የክርስቶስን መዓዛ በየስፍራው የሚገልጥ እንጂ ወንጌልን ለትርፍ የሚሸቃቅጥ (Retailer) አይደለም ።
- የአገልግሎት ብቃት ምንጭ፦ ብቃታችን "በቅቻለሁ" ከሚል ግላዊ ወኔ ሳይሆን፣ እኛን አገልጋዮች አድርጎ ከሾመን ከእግዚአብሔር ምሕረትና ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚመነጭ መሆኑን እንማራለን ።
- የሚልቀው የዐዲስ ኪዳን ክብር፦ በፊደልና በድንጋይ ጽላት ላይ ከተጻፈው የብሉይ ኪዳን አገልግሎት ይልቅ፣ መንፈስ ቅዱስ በልብ ጽላት ላይ የሚጽፈውና ሰዎችን የሚለውጠው የዐዲስ ኪዳን አገልግሎት ክብር እንዴት እንደሚበልጥና እንደማይሻር እናያለን ።
- በተገለጠ ፊት ማገልገል፦ እንደ ሙሴ ፊትን በመሸፈን ሳይሆን፣ የጌታን ክብር እያየንና እያንጸባረቅን ወደ እርሱ መልክ እንዴት እንደምንለወጥ (Transformation) እንመለከታለን ።
- ቅርጸ-መስቀላዊነት (Cruciformity)፦ አገልግሎት ማለት የክርስቶስን ሞት በሰውነት ተሸክሞ መዞርና ፣ ራስን ዝቅ አድርጎ ለሌሎች ጥቅም መኖር (Selfless service) እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ይህ ትምህርት ለማን ነው?

- ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች፦ የአገልግሎታቸውን ዓላማ፣ ንጽህና እና የትኩረት አቅጣጫ ለመፈተሽና ለማስተካከል ለሚፈልጉ።
- ለወንጌል ሰባኪዎችና አስተማሪዎች፦ ወንጌልን "ሳይቀላቅሉ" እና "ሳይሸቃቅጡ" በቅንነትና በእግዚአብሔር ፊት በተጠያቂነት ለማገልገል ለሚሹ።
- ለማንኛውም ክርስቲያን፦ ክርስትና ማለት በመስቀሉ መንገድ (Way of the Cross) መጓዝ እንደሆነ ለመረዳት ለሚፈልግ ሁሉ።
ማሳሰቢያ
ይህ ስልጠና አገልግሎትን እንደ "ቢዝነስ" ወይም "የግል ዝና ማግኛ" ከሚቆጥሩ የተሳሳቱ ልምምዶች በመውጣት፣ ኢየሱስን ማዕከል ያደረገ (Christ-Centered) እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚከናወን አገልግሎትን ለመታጠቅ የሚረዳ ነው።
ይህንን ወሳኝ የአገልጋዮች ስልጠና ወደ አጥቢያዎ ይውሰዱ። ከስር ባለው ሊንክ በመመዝገብ ፕሮግራም ያስይዙ።