የሚናገረው አምላክ፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣንና መሠረታዊ ባሕርይ
ስለ ሴሚናሩ
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን በጥያቄ ምልክት ውስጥ በገባበትና ብዥታ በበዛበት በዚህ ዘመን፣ ቤተክርስቲያን ወደ እውነተኛው መሠረቷ መመለስ አለባት። ይህ ሴሚናር ከተለመዱት የአጠናን ዘዴዎች (Study methods) አልፎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ "ምንድን ነው?" ወደሚለው መሠረታዊ የእግዚአብሔር ድምፅነት ይወስደናል።
“የማይናገር አምላክ፤ ይቅር ማለት፣ ቃል ኪዳን መግባት፣ ወይም ማዘዝ አይችልም” ።
ይህ ስልጠና ምእመናን መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አንድ የማይንቀሳቀስ መጽሐፍ ከመመልከት አልፈን፣ የሥሉስ አምላክ ንቁ ንግግር (Active Speech) አድርገን እንድንቀበል ይጋብዛል። የተሳሳቱ አመለካከቶችን በመፍታት፣ በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-መለኮት እንገነባለን።
በሴሚናሩ የሚዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-
- የሚናገረው አምላክ (The God Who Speaks)፦ እግዚአብሔር በባሕርይው "የሚናገር አምላክ" እንደሆነና በቃሉ አማካኝነት እንደሚፈጥር፣ እንደሚያድንና እንደሚያስተዳድር እንማራለን ።
- ቃሉና መንፈሱ (Word & Spirit)፦ መጽሐፉን በትንፋሹ የሰጠው መንፈስ ቅዱስ፣ ዛሬም ቃሉን ስናነብ የሚያበራልን ያው መንፈስ ነው። በ"አፊዎት" (Inspiration) እና በ"አብርሆት" (Illumination) መካከል ያለውን ልዩነትና አንድነት እንረዳለን ።
- ክርስቶስ - የመጨረሻው ቃል፦ የእግዚአብሔር መገለጥ በታሪክ ሂደት ደረጃ በደረጃ እያደገ መጥቶ (Progressive Revelation)፣ የመጨረሻው ቃል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ፍጻሜውን እንዳገኘ እናያለን ።
- ቃሉ የፈጠራት ማኅበር፦ ቤተክርስቲያን በቃሉ ላይ ጌታ አይደለችም፤ ይልቁንም ቃሉ ቤተክርስቲያንን ፈጥሯልና ለቃሉ ትገዛለች ።
- የዘመኑ ተግዳሮቶች፦ "መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል ይዟል (Contains)" ወይስ "መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው (Is)?" ለሚሉና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ እንሰጣለን ። እንዲሁም "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" (Sola Scriptura) የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ በአግባቡ እንረዳለን ።
ይህ ትምህርት ለማን ነው?
- ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች፦ የአገልግሎታቸውን ሥነ-መለኮታዊ አከርካሪ ለማጠንከር።
- ለሰንበት ት/ቤት አስተማሪዎች፦ ስለሚያስተምሩት ቃል መለኮታዊ ምንጭና ሥልጣን ጥልቅ መረዳት ለመያዝ።
- ለማንኛውም አማኝ፦ እግዚአብሔርን ማወቅ የመዳናችን የመጨረሻ ግብ እንደመሆኑ፣ ከ"መረጃ ሰብሳቢነት" ወደ "ሕያው ግንኙነት" ለማደግ ለሚፈልግ ሁሉ ።
ማሳሰቢያ
ይህ ሴሚናር የአእምሮ እውቀትን (Academic knowledge) ብቻ የሚጨምር ሳይሆን፣ ራሱን በቃሉ የገለጠውን አምላክ እንድናውቅና በፊቱ በትሕትና እንድንቀርብ የሚጠራ ነው። ትምህርቱ በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ የድነት ታሪክ (Redemptive History) ላይ የተመሠረተ ነው ።
ይህንን ወሳኝ ትምህርት ወደ አጥቢያዎ ይውሰዱ። ሳከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ፕሮግራም ያስይዙ።