
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት
እግዚአብሔር ራሱን በታሪክ ሂደትና በደረጃ እንዴት እንደገለጠ ይመረምራል
እግዚአብሔር ራሱን የገለጠልን በአንድ ጊዜ አይደለም። መገለጡ በጊዜ ሂደት ውስጥ ቀስ በቀስና ደረጃ በደረጃ እያደገ መጥቶ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜውን አግኝቷል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ መለኮት ለዚህ የዕድገት ሂደት ልዩ ትኩረት ይሰጣል።”
መጽሐፍ ቅዱስን አንድ ወጥ ሙሉ አካል አድርጎ ይመለከተዋል
መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ከማይቃረን ከአንድ መለኮታዊ ጸሐፊ የተገኘ በመሆኑ፣ ይህ ጥናት መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አንድ ወጥ ሙሉ አካል አድርጎ ይመለከተዋል። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን አንድነት ፈልገን እንድናገኝና በግልጽ እንድናብራራ ይረዳናል
ትኩረቱ በድነት ታሪክ ላይ ነው
፤ ይህም ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ውድቀት፣ ቤዛነት እና በኢየሱስ ክርስቶስ እስከሆነው ፍጻሜ ድረስ፣ እግዚአብሔር ያደረጋቸው የማዳን ሥራዎች እውነተኛ ታሪክ ነው። ይህ የታሪክ መስመር የመላው መጽሐፍ ቅዱስ አከርካሪ ነው።
ከቅዱሳት መጻሕፍት በመነሣት (inductively) ይሠራል
ይህ ጥናት በተቀዳሚነት ከጽሑፉ በመነሣት (inductively) ይሠራል እንጂ በታሪክ ውስጥ የዳበረውን ታሪካዊ ነገረ-መለኮት ወይም በስልት የተጠናከረውን ስልታዌ መዋቅር ይዞ አይቀርብም። ውጪ መዋቅር በላዩ ላይ ከመጫን ይልቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የራሱን አጀንዳና (bible’s own category) የትራኬ አቅጣጫ እንዲወስን ይፈቅዳል። ይህም ማለት ‘ምንባቡ በትክክል ምን ይላል?’ እና ‘ጸሐፊው በተናገረው ቃል ምን ማለቱ ነበር?’ የሚለውን ለመረዳት እንተጋለን ማለት ነው።
ብሉይና ሐዲስ ኪዳንን ያነጋግራል
ይህ ጥናት ብሉይ እና ሐዲስ ኪዳንን ያስተሳስራል። ይህም የኋለኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የቀደሙትን እንዴት እንደጠቀሱ በማስተዋል፣ ትንቢትንና ፍጻሜን በመከታተል (fulfillment)፣ እንዲሁም ከብሉይ እስከ ሐዲስ ድረስ የተዘረጕ ዐውደ-ዕሳቤውችን በጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያላቸውን ዕድገት (thematic progressions) ይመረምራል። በዚህ ሂደት ውስጥ ምን ቀጠለና ምን ቀረ የሚለውን (continuity & discontinuity) ያገናዝባል።
በመጨረሻ በክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለተሰጠንና ሥልጣን ላለው የእግዚአብሔር መገለጥ በትህትና ምላሽ እንድንሰጥ ያበረታታናል። ሁላችንም በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት በዕውቀት እናድግ ዘንድ፣ ይህም ለእግዚአብሔር ቃል ያለንን አክብሮት እንዲያቀጣጥልና ከእርሱ ጋር ያለንን አካሄድ እንዲያጠነክርልን ምኞቴ ነው!