ማስተማር . ማስታጠቅ . መላክ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት
ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት የቅዱሳት መጻሕፍትን ‘ትልቅ ስዕል’ መመልከት ነው። ይህም እያንዳንዱን ጥቅስ ወይም ታሪክ ለየብቻ ነጣጥለን ከማየት ይልቅ፣ ሁሉም ክፍሎች ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ተሳስረው እንዴት አንድ ወጥ የሆነውን የእግዚአብሔርን የድነት-ታሪክ የምናይበት መንገድ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት ብሉይ ኪዳን እንዴት ከአዲስ እንደሚገጣጠም በማስተዋል፣ እግዚአብሔር በቃሉ በኵል ዛሬ ለእኛ የሚናገረውን መልእክት በግልጽ እንድነሰማ ይረዳናል።
በዚህ ድረ-ገጽ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በምናደርገው ጉዞ፣ ለህይወታችንና ለቤተ ክርስቲያናችን የሚሆኑ ጥልቅ እውነቶችን ለማስረዳት እንሻለን። ስለዚህ፣ ለቤተ ክርስቲያን ይህንን ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ ልናስተዋውቃችሁ እንወዳለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት ለነገረ-መለኮት መምህራንና ተቋማት ብቻ የተሰጠ ሳይሆን፣ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽና ለእያንዳንዱ አማኝ የሚጠቅም ኀይለኛ መሣሪያ እንደሆነ አንጠራጠርም።

ትኩረታችን በቤተ ክርስቲያን ላይ ነው
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እናምናለን። ይህ ጥናት የአእምሮ እውቀት ብቻ አይደለም። ይልቁንም፣ ለአማኞች በተናጠልና ለቤተ ክርስቲያን ህይወት በጥቅል አያሌ ተግባራዊ ጠቀሜታ አለው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት፣ ባለ ብዙ ገጽታና አስደናቂ ባለጠግነት ባለው ቃሉ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ዐሳብ እንድናይ በማድረግ ሕይወታችንን ይለውጣል።
በመጨረሻም በክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለተሰጠንና ሥልጣን ላለው የእግዚአብሔር መገለጥ በትህትና ምላሽ እንድንሰጥ ያበረታታናል። ሁላችንም በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት በዕውቀት እናድግ ዘንድ፣ ይህም ለእግዚአብሔር ቃል ያለንን አክብሮት እንዲያቀጣጥልና ከእርሱ ጋር ያለንን አካሄድ እንዲያጠነክርልን ምኞቴ ነው!
እየተሰጡ ያሉ ትምህርቶች
Currently, we are opening up the following teaching series. If your church would like to host one of these classes, please contact us.
Equip Your Church with Deep, Life-Changing Theology.
Flexible Formats to Fit Your Schedule
What You Get

የሚናገረው አምላክ፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣንና መሠረታዊ ባሕርይ
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን በጥያቄ ምልክት ውስጥ በገባበትና ብዥታ በበዛበት በዚህ ዘመን፣ ቤተክርስቲያን ወደ እውነተኛው መሠረቷ መመለስ አለባት። ይህ ሴሚናር ከተለመዱት የአጠናን ዘዴዎች (Study methods) አልፎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “ምንድን ነው?” ወደሚለው መሠረታዊ የእግዚአብሔር ድምፅነት ይወስደናል።

የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናንና አተረጓጎም
(Biblical Interpretation)
የእግዚአብሔርን ቃል “በትክክል የሚያስረዳ” (2 ጢሞ 2:15) አገልጋይና አማኝ ለመሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት በትክክል እንደሚያዝ መረዳት ወሳኝ ነው። ይህ ሴሚናር ከዘልማዳዊ ንባብ ወጥተን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ዐውድ፣ የሥነ-ጽሑፍ ዓይነት እና የቃላት ፍቺ በመመርመር፣ የጸሐፊውን ሐሳብ እንዴት ማግኘት እንደምንችል በተግባር የሚያስታጥቅ ነው።

ቅርጸ-መስቀላዊ አገልግሎት፡ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ጥሪና ክብር
በዘመናችን ስለ “አገልግሎት” ያለን ግንዛቤ በዝና፣ በገንዘብና በውጫዊ ስኬት መለኪያዎች ተበርዟል። ብዙዎች “ለዚህ አገልግሎት የሚበቃ ማን ነው?” ብለው ከመጠየቅ ይልቅ፣ በራሳቸው ብቃት እየተመኩ ወንጌልን ወደ ንግድ ሸቀጥነት (Peddling) የቀየሩበት ጊዜ ላይ ነን። ይህ ሴሚናር፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ እንደሚያስተምረው፣ አገልግሎት ማለት የግል ስኬት መሰላል ሳይሆን “የተሰቀለውን ክርስቶስን” በመስበክ ፣ አገልግሎታቸው የመስቀሉን ቅርጽ (Cruciformity) እንዴት መላበስ እንዳለበት በሰፊው ይዳስሳል።

የተራራው ስብከት
(The Sermon on the Mount)
“የተራራው ስብከት” የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ጫፍ እና የክርስትናዊ ሥነ-ምግባር መሠረት ነው።
ብዙዎቻችን እነዚህን ምንባባት (ማቴዎስ 5 – 7 ) ብናውቃቸውም፣ ወደ ጥልቀቱ ወርደን የመንግሥቱን የኑሮ ዘይቤ ምንነት ግን አልተረዳንም።
ይህ ሴሚናር፣ ኢየሱስ በምድር ላይ ሊመሠርተው ስለመጣው መንግሥት ባህርይ፣ ስለ እውነተኛ ጽድቅ እና ስለ ኪዳኑ ሕዝብ አኗኗር ያስተማረውን ሕያው ቃል የምንመረምርበት ነው።